1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኬንያ እና የተደቀነባት ችግር

ቅዳሜ፣ ታኅሣሥ 5 2006

ኬንያ ከብሪታንያ ቅኝ አገዛዝ የተላቀቀችበትን 50 ኛ ዓመት የነፃነት በዓል ባከበረችበት ባለፈው ሀሙስ ወደብ ከተማ ሞምባሳ ውስጥ ሁለት ብሪታንያውያን ቱሪስቶችን ያሳፈረ አንድ ላንድ ክሩዘር መኪና ላይ የተወረወረ ቦምብ መኪናውን መቶ ሳይፈነዳ መሬት መውደቁን የሞምባሳ ፖሊስ ኃላፊ ማስታወቃቸው ይታወሳል።

https://p.dw.com/p/1AZXj
Kenia Unabhängigkeitstag 12.12. 2013
ምስል Simon Maina/AFP/Getty Images

ፖሊስ ይኸው የከሸፈው የቦምብ ጥቃት ግን ከበዓሉ ጋር ምንም ግንኙነት እንደሌለው ገልጾዋል። ከሶማሊያአሸባብ ማፂ ቡድን በኩል ጣላሉ ተብለው ሚያሰጉ ጥቃቶች የተነሳ ዋነኛ የገቢ ምንጭዋ በቱሪዝም ላይ በተመሰረተው በኬንያዋ የወደብ ከተማ ሞምባሳ እአአ በ2013 ዓም የመጀመሪያዎቹ አምስት ወራት የውጭ ገር ጎብኚዎች ቁጥር 15 በመቶ መቀነሱን የሀገሪቱ መንግሥት አስታውቋል። ይህም የሚያሳየው የፀጥታው ሁኔታ በዚህ በ50ኛ የነፃነት ዓመትም ላይ በኬንያ ከተደቀኑት ችግሮች መካከል አንዱ መሆኑን ነው። በወቅቱ በኬንያ በተለያዩት ጎሣዎች መካከል ግዙፍ ውጥረት ማስከተሉን በናይሮቢ የሚገኙት የፖለቲካ ተንታኝ ማርቲን ኦሎ አስታውቀዋል።

Kenia Unabhängigkeitstag 12.12. 2013
ምስል Simon Maina/AFP/Getty Images

« እርግጥ፣ በጎሣዎች መካከል የሚታየው የመቀናቀን ተግባር፣ ማለትም፣ ጎሠኝነት ዛሬም ኬንያ ውስጥ ብዙ የሚያነጋግር ጉዳይ ነው። እና ፕሬዚደንቱ ከትናንት በስቲያ ባደረጉት ንግግር ላይ ይህ ችግር መኖሩን በማረጋገጥ ዋናው አጀንዳቸው ብሔራዊ አንድነት መፍጠር መሆኑን አስታውቀዋል። ይህ ማለት ኬንያ መከፋፈልዋን ፣ በኬንያ ጎሠኝነት መስፋፋቱን፣ ኬንያ የ42 ጎሣዎች የሚኖሩባት ሀገር መሆንዋን በማስታወቅ እነዚህን የተለያዩ ቡድኖችን አንድ ለማድረግ ይፈልጋሉ። ጎሠኝነት እና አሉታዊው ነገደኝነት ኬንያውያን ሊያስወግዱት የሚገባ ትልቅ ችግር እንደሆን ይገኛል። »

ጎሠኝነት ብቻ አይደለም ኬንያ ውስጥ ከ50 የነፃነት ዓመታት በኋላ ጎልቶ የሚታየው ሌላ ችግር ደግሞ በድሀው እና በሀብታሙ መካከል ያለው ግዙፍ ልዩነት ነው። ፕሬዚደንት በዚሁ ጎልቶ በሚታየው የእኩልነት መጓደልም ችግር አንፃር ርምጃ መውሰድ አስፈላጊ መሆኑንም በንግግራቸው በግልጽ አስቀምጠውታል። ሁሉን እኩል ተጠቃሚ የሚያደርግ አሳታፊ ሥርዓት ለመፍጠር ዕቅድ እንዳላቸው መገለጻቸው አዎንታዊ ቢሆንም፣ እንደ ማርቲን ኦሎ አስተያየት፣ ይህ ዕቅድ ገሀድ ይሆን ዘንድ ብዙ ሊሰራ እንደሚገባ እና ግዙፍ መዋዕለ ንዋይ ስራ ላይ መዋል ይኖርበታል።

Kenia 50 Jahre Unabhängigkeit
ምስል DW/A. Kiti

« የኬንያ ኤኮኖሚ ሂደት በደህና ሁኔታ ላይ የሚገኙትን ይበልጡን ሀብታም፣ የሌላቸውን ደግሞ ይበልጡን ድሀ የሚያደርግ። እርግጥ፣ ሁኔታውን ማሻሻል የሚቻልበት ዕድል አለ። ግን፣ በሀገሪቱ ሁሉን እኩል የሚያሳትፍ የልማት ሂደትእንዲነቃቃ ከተፈለገ ከፖለቲካ መሪዎች፣ ከሕግ አውጪው አካል እና ከኤኮኖሚ ው አንቀሳቃሾች በኩል ሁነኛ ዕቅድ መውጣት ይኖርበታል። »

ከዚህ በተጨማሪም በአሁኑ ጊዜ በስብዕና አንፃር ወንጀል ፈፀመዋል በሚል ጥርጣሬ በዓለም አቀፉ የጦር ወንጀል ተመልካች ፍርድ ቤት ክስ ስለተመሰረተባቸው ፕሬዚደንት ኡሁሩ ኬንያታ እና ምክትላቸው ዊልያም ሩቶ ችሎት በሀገሪቱ ገፅታ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ አሳርፎዋል፣ በመሆኑም ይላሉ ማርቲን ኦሎ ፣ በሀገሪቱ የወደፊት አካሄድ ላይ አሉታዊ ሚና ስለሚኖረው በሕዝቡ ዘንድ ትልቅ ቅሬታ የፈጠሩ ጉዳዮች ናቸው።

« የአፍሪቃ ህብረት በዓለም ዓቀፉ የጦር ወንጀል ተመልካች ፍርድ ቤት (ICC) አኳያ የያዘው አቋም እና በኬንያ ከፍተኛ ባለስልጣናት ላይ የመሠረተው ክስ ለአንድ ዓመት እንዲያዘገይ ተመድ የፀጥታዉ ምክር ያቀረቡትን ማመልከቻ ውድቅ ያደረገበት ውሳኔ፣ ይህ ሁሉ የሁለቱን መሪዎች አሰራርን እና ኬንያውያንን መሪዎቻቸው ሊሰጡዋቸው የሚገባቸውን አገልግሎት ማግኘት አለማግኘታቸው ላይ ተፅዕኖ እንደሚያሳርፍ የሚጠቁም ነው፤ ጉዳዩ በፍርድ ቤት የተያዘ እንደመሆኑ መጠን ተከሳሾቹ መሪዎች በነፃ ሊለቀቁ ወይም ሊፈረድባቸው ስለሚችል መስጋታቸው አልቀረም። »

አርያም ተክሌ

ልደት አበበ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ