1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ካታ ኢዱሊስ(ጫት)

ማክሰኞ፣ ኅዳር 30 2001

የአእምሮ መታወክ ወይም መረበሽ ጫት ከሚያስከትላቸዉ የጤና ችግሮች ዋነኛዉን ስፍራ ይይዛል።

https://p.dw.com/p/GCRI
ቃሚዉ እርሻ ዉስጥ (ደደር)
ቃሚዉ እርሻ ዉስጥ (ደደር)ምስል AP
በሳይንሳዊ አጠራሩ ካታ ኢዱሊስ ይባላል። ኢትዮጵያ ዉስጥ ጫትም ካትም የሚሉት አሉ፤ ለኬንያዉያን ደግሞ ሚራ ነዉ ስሙ። የሚበቅለዉ በብዛት በኢትዮጵያ፤ የመንና ሳዉዲ አረቢያ ነዉ። አፍሪቃ ዉስጥም ከኢትዮጵያ አንስቶ እስከ ደቡብ አፍሪቃ እንዲሁ ይገኛል። በአገራችን በተለይ ከፍታቸዉ ከ1400 እስከ 2100 ሜትር በሆነ አካባቢዎች መብቀል ሲችል አስተዳደጉ ከቁጥቋጦ አንስቶ እስከ ትልቅ ዛፍ ቁመት ሊደርስ ይችላል።