ከፓሪሱ ስምምነት አወጣጥ ሂደት
ማክሰኞ፣ ሰኔ 6 2009ማስታወቂያ
የቡድን ሰባት አባል ሃገራት የሆኑት ሌሎቹ ማለትም የካናዳ፣ የጣሊያን፣ የፈረንሳይ፣ የጀርመን፣ ጃፓን እና ዩናይትድ ኪንግደም ማለትም ብሪታንያ የአካባቢ ጥበቃ ሚኒስትሮች የፓሪሱ የሙቀት አማቂ ጋዞች ልቀትን ቅነሳ የሚመለከተዉ ስምምነት ወደኋላ የማይመለስና ዳግም ለድርድር የማይቀርብ ጉዳይ መሆኑን በአፅንኦት ገልጸዋል። ዩናይትድ ስቴትስ ከዚህ ስምምነት እወጣለሁ ብትልም እንዲህ ካለዉ ዓለም አቀፋዊ ስምምነት የወጣጡ ሂደት ቀላል እና አጭር እንደማይሆን በካናዳ ካልጋሪ ዩኒቨርሲቲ የአካባቢ ተፈጥሮ ዲዛይን ፋኩልቲ ተባባሪ ፕሮፌሰር እና የዘርፉ ተመራማሪ፤ ለሆኑት ለዶክተር ጌታቸዉ አሰፋ አጽንኦት ሰጥተዋል። የዋሽንግተን ከዚህ ስምምነት ራሷን ማግለል ምን ያስከትላል? የአወጣጧስ ተግባራዊነት ለሚሉት ተያያዥ ጥያቄዎች ማብራሪያ ከድምጽ ዘገባዉ ማድመጥ ይችላሉ።
ሸዋዬ ለገሠ
አዜብ ታደሰ