ከፍተኛ የታክስ ጭማሪ እና ሮሮ
ረቡዕ፣ ሰኔ 28 2009ማስታወቂያ
ከአዲስ አበባ በደረሰን ዘገባ መሠረት ግብር ከፋዮች ከአቅም በላይ እጅግ ከፍተኛ መጠን ያለው ክፍያ ተጥሎበቸው እያማረሩ ነው። ከዚህ ቀደም እስካሁን ድረስ በዓመት 3000 ብር ነበር የምከፍለው። አሁን ደግሞ በቀን ገቢ 1800 ብር ዓመታዊ አምስት መቶ ሺህ ብር በላይ አድርገውት ፣አይደለም መክፈል ምንም ማድረግ አንችልም» ይላሉ አንድ ነጋዴ። ከዓረብ ሀገር ከመጣች ገና አራት ወር የሆናት ደግሞ የግብሩ መጠን ከአቅሟ በላይ እንደሆነ በመግለጥ ወደ ዓረብ ሀገር ዳግም ለመሰደድ መቁረጧን እንባ እየተናነቃት ለአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ተናግራለች።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ኂሩት መለሰ