1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የገንዘብ ማሸሽ ቅሌት 

ሰኞ፣ ጥቅምት 27 2010

ከ67 ሀገራትየተውጣጡ 400 ጋዜጠኞች ይፋ ያደረጓቸው 13,4ሚልዮን ህቡዕ ሰነዶች በየሀገሮቻቸው ግብር እንዳይከፍሉ ሲሉ ገንዘባቸውን ወደውጭ ያሸሹ ከፍተኛ የመንግሥት ባለስልጣናትን፣ ቱጃሮችንና የንግድ ተቋማትን ስም አጋለጡ። ፓራዳይዝ ፔፐርስ በሚል መጠሪያ ስር የወጡትን ሰነዶች ትናንት ያሾለከው የጀርመናውያኑ ዕለታዊ ዚውድዶይቸ ጋዜጣ ነው።

https://p.dw.com/p/2n7nk
Paradise Papers | Symbolbild Steueroasen
ምስል picture-alliance/Klaus Ohlenschläger

ፓራዳይዝ ፔፐርስ

ፓራዳይዝ ፔፐርስ በሚል መጠሪያ ስር  በወጡት ሰነዶች መሰረት፣ የገቢ ግብር ላለመክፈል በሚል  ገንዘባቸውን ቀረጥ ወደማያስከፍሉዋቸው ሀገራት አሸሽተዋል በሚል ስማቸው ከተጠቀሱት መካከል የእንግሊዝ ንግሥት ኤልሳቤጥ ዳግማዊት፣ የካናዳ ጠቅላይ ሚንስትር ጃስቲን ትሩዶ፣ የዩኤስ አሜሪካ የንግድ ሚንስትር ዊልበር ሮስ፣  ሌሎች የዩኤስ ካቢኔ አባላት ፣ ከአስር የሚበልጡ የፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ አማካሪዎች እና በምርጫ ዘመቻ ገንዘብ የሰጡዋቸው  ግለሰቦች፣ እንዲሁም፣  ናይክ፣ አፕል፣ ፌስቡክ እና ኡበርን የመሳሰሉት የንግድ ተቋማት ይገኙባቸዋል።

መክብብ ሸዋ/አርያም ተክሌ

ሂሩት መለሰ