ከፊሉ የምርጫ ውጤት እና የመድረክ አስተያየት
ሐሙስ፣ ግንቦት 20 2007ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከአራት ቀናት በፊት በተካሄደው ሀገራዊ ምርጫ እስካሁን ከክልሎች በደረሰው ከፊል ውጤት ገዢዉ ፓርቲ ኢ ህ አ ዴ ግ እና አጋር ድርጅቶች ለሕዝብ ተወካዮች እና ለክልል ምክር ቤቶች አብላጫዉን ድምፅ ማግኘታቸዉን በትናንቱ ዕለት መግለጹ ይታወቃል። በቦርዱ መግለጫ መሠረት፣ ኢ ህ አ ዴ ግ እና አጋር ድርጅቶች ከ547 የምክር ቤቶች መንበሮች 442 አግኝተዋል። የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ ፣ በምህፃሩ መድረክ ይህንኑ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ያወጣውን ከፊል ውጤት፣ የምርጫው ሂደት ሰላማዊ አልነበረም በማለት እንደማይቀበለው ለዶይቸ ቬለ ገልጾዋል።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
አርያም ተክሌ
ሂሩት መለሰ