ከጣሊያን ወደ ስዊድን የተላኩ ኤርትራውያን 28 መስከረም 2008ዓርብ፣ መስከረም 28 2008ስዊድን በዛሬው ዕለት ከጣሊያን 19 ኤርትራውያን ስደተኞችን ወደ ሀገሯ ማስመጣቷ ተገለጠ። የአውሮጳ ሕብረት ስደተኞችን በአባል ሃገራቱ ለማከፋፈል በቅርቡ ስምምነት ላይ መድረሱ ይታወሳል።https://p.dw.com/p/1Glboምስል Reuters/R. Casilliማስታወቂያ[No title]To play this audio please enable JavaScript, and consider upgrading to a web browser that supports HTML5 audio ኤርትራውያኑ ስደተኞችን የጫነው የጣሊያን ፖሊስ አውሮፕላን ከመዲናዪቱ ሮም በመነሳት ሰሜናዊ ስዊድን ውስጥ ወደምትገኘው ሉሌያ የተባለች አካባቢ መብረሩ ተዘግቧል። ስደተኞቹ ስዊድን ውስጥ ተመዝግበው የጥገኝነት ጥያቄያቸው በሒደት መታየት እንደሚጀምርም ተገልጧል። .የስቶክሆልሙ ወኪላችን ቴዎድሮስ ምሕረቱ ዝርዝር ዘገባ አለው። ቴዎድሮስ ምሕረቱ ማንተጋፍቶት ስለሺ ኂሩት መለሰ