ከጋምቤላ ከታገቱት 14 መመለሳቸው
ሰኞ፣ ግንቦት 1 2008ማስታወቂያ
ከሶስት ሳምንት በፊት ከደቡብ ሱዳን መጡ በተባሉ የሙርሌ ጎሳ አባላት ከጋምቤላ ከታገቱት ህጻናት መካከል 14ቱ መመለሳቸውን የመንግሥት መገናኛ ብዙሃን ዛሬ ዘግበዋል ። ተመለሱ ስለተባሉት ህጻናት የኢትዮጵያ መንግሥት የኮምኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ለዶቼቬለ በሰጡት ቃለ ምልልስ ህጻናቱን የማስመለሱ ሥራ ውጤት እያመጣ መሆኑን ከመናገር ውጭ ዝርዝር ሁኔታዎችን አልገለጹም። ሃላፊው ህጻናቱን ማስለቀቁ የዘገየው ጉዳት ሳይደርስባቸው ወደ ቤተሰቦቻቸው እንዲመለሱ በሚደረገው ጥንቃቄ መሆኑን አስታውቀዋል።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ