ከበሽታው የተረፉትን መደገፍ
ዓርብ፣ የካቲት 13 2007ማስታወቂያ
የኢቦላ ኅመምተኛ የነበረ ሰው የበሽታው ምልክቶች ከሰውነቱ ላይ ከጠፉ ከጥቂት ቀናት በኋላ የበሽታው አስተላላፊነቱ ያከትማል፤ በእርግጥ ተሐዋሲው በዘር ፈሣሹ ውስጥ ለበርካታ ሣምንታት መቆየት መቻሉ መዘንጋት የለበትም። ስለዚህም ከኢቦላ በሽታ የተረፉ ሰዎች የኢቦላ ተሐዋሲ ምልክቶች ከሰውነታቸው ላይ ከጠፉበት ጊዜ አንስቶ ቢያንስ ለሚቀጥሉት ሦስት ወራት ኮንዶሞችን ሊጠቀሙ ይገባል።
ከኢቦላ በሽታ የተረፉ ሰዎች ደም በኢቦላ ተሐዋሲ ዳግም እንዳይጠቁ የሚያስችሉ የሰውነት በሽታ ተከላካዮችን የያዘ ነው። እነዚህ የበሽታ ተከላካዮች የኢቦላ ኅመምተኞችን ለመርዳት ጥቅም ላይ ሊውሉ ይችላሉ።
ከኢቦላ በሽታ የተረፉ ሰዎችን መሸሽና እና ማግለል አያስፈልግም። ርዳታ ያሻቸዋል። እጅግ በጠና ኅመም ተሠቃይተዋል፤ ብዙዎቹ በተሐዋሲው የቤተሰብ አባላቸውን አጥተዋል። ኅብረተሰቡ በተቻለ መጠን ሊደግፋቸው እንጂ፥ ጭራሽ መከራቸውን ሊያባባስ አይገባም።