ከሳዑዲ አረቢያ የሚመለሱ ኢትዮጵያዉያን
ሐሙስ፣ ሰኔ 22 2009ማስታወቂያ
የሳዑዲ አረቢያ መንግስት ከሐገሩ እንዲወጡ ያስገደዳቸዉ ኢትዮጵያዉያን ብዙ ሳይንገላቱ ወደ ሐገራቸዉ እንዲገቡ ለማድረግ የጀመረዉን ጥረት እንደሚቀጥል የኢትዮጵያ መንግሥት አስታወቀ።የሳዑዲ አረቢያ መንግሥት «ሕገ-ወጥ» ያላቸዉ የዉጪ ዜጎች ከሐገሩ እንዲወጡ የሰጠዉ ቀነገደብ ቢጠናቀቅም በብዙ ሺሕ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዉን አሁንም ወደ ሐገራቸዉ አልተመለሱም።የኢትዮጵያ የዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር ዛሬ እንዳስታወቀቁ ሳዑዲ አረቢያ የሰጠችዉን ቀነ-ገደብ እንድታራዝም የኢትዮጵያ መንግሥት በድጋሚ ጠይቋል።
ዮኃንስ ገብረ እግዚአብሔር
ነጋሽ መሐመድ
አርያም ተክሌ