ከሳዉዲ የተመለሱ ኢትዮጵያዉያን
ረቡዕ፣ ኅዳር 11 2006ማስታወቂያ
ዘገባዎች እንደሚሉትም እስካሁን 60 ሺህ ያህሉን ሸኝታለች ፍተሻና ወደየሀገር መመለሱም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ነዉ የሀገር ዉስጥ ሚኒስትሩ ያመለከቱት። በተመሳሳይ ሁኔታ እዚያ የሚገኙ ኢትዮጵያዉያን እንዲሁ ወደሀገር መመለስ መጀመራቸዉ ተሰምቷል። ዛሬም በሪያድና ሌሎች የሳዉዲ ግዛቶች ከዚያ የመዉጫ ቀናቸዉን እየጠበቁ፤ አደጋ ላይነንና ድረሱልን የሚሉት ወገኖች ቁጥራቸዉ ቀላል ባይሆንም። የኢትዮጵያ መንግስት ችግር ላይ ያሉት ዜጎች በቀጣይ ሳምንታት ዉስጥ ተጠቃለዉ ሊገቡ እንደሚችሉ ገልጿል። እስካሁንም ከአራት ሺህ በላይ ገብተዋል። የአዲስ አበባዉ ዘጋቢያችን ጌታቸዉ ተድላ ኃይለጊዮርጊስ ወደሀገር ቤት መመለስ ከቻሉት አንዳንዶቹን በማነጋገር ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል።
ጌታቸዉ ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ
ሸዋዬ ለገሠ