1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ከሰሃራ በታች ኢንተርኔትን የዘጉ አፍሪቃ ሃገራት

ሰኞ፣ ጥር 8 2009

ከሰሃራ በታች ካሉ ሃገራት ኢትዮጵያ የኢንተርኔት አገልግሎትን በመገደብ ቀዳሚዋ ሀገር መሆንዋን አንድ የዲጂታል መብት ተቆጣጣሪ ድርጅት አስታወቀ። ድርጅቱ ከአስር ቀን በፊት ይፋ ባደረገዉ መረጃ፤ በተሰናበትነዉ በጎርጎሮሳዊዉ 2016 ዓ.ም ኢትዮጵያ አራት ጊዜ በዜጎቿ ላይ መረጃን እንዳያገኙም ሆነ እንዳያስተላልፉ ኢንተርኔትን ዘግታለች።

https://p.dw.com/p/2Vs7c
Yahoo Logo Schriftzug Computer
ምስል picture-alliance/dpa/M. Nelson

በተሰናበትነዉ በጎርጎሮሳዊዉ 2016 ዓ.ም ከሰሃራ በስተ ደቡብ ካሉ ሃገራት ኢትዮጵያ አራት ጊዜ በዜጎቿ ላይ መረጃን እንዳያገኙም ሆነ እንዳያስተላልፉ ኢንተርኔትን ዘግታለች። ከኢትዮጵያ ሌላ፣ ጋምቢያንና ዩጋንዳ ሁለት ጊዜ ኢንተርኔትን የዘጉ ሲሆን ቻድ፤ ዴሞክራቲክ ሬፓብሊክ ኮንጎ፤ ጋቦን፤ ማሊ፤ ዛምቢያ እና ዚምባቤ ለዜጎቻቸዉ አንድ ጊዜ የኢንተርኔት አገልግሎትን አቋርጠዉ እንደነበር ድርጅቱ ይፋ ያደረገዉ ጥናት ያመለክታል። እንደ ጥናቱ፤ ሃገራቱ በዜጎቻቸዉ ላይ የኢንተርኔት አገልግሎትን ያገዱት በሃገራቱ አንዴም ምርጫ አልያም ደግሞ ሕዝባዊ ተቃዉሞን የመሳሰሉ ቁልፍ የሆኑ ከፍተኛ ፖለቲካዉ ክንዉኖች በታዩበት ወቅት ነዉ። የዋሽንግተን ዲሲዉ ወኪላችን መክብብ ሸዋ  የዲጂታል መብት ተቆጣጣሪዉን ድርጅት የአፍሪቃ ጉዳዮች ዋና ተጠሪ ዴጄ ኦልኮቱንን አነጋግሮ ዝርዝር ዘገባዉን እንዲህ ልኮልናል። 


መክብብ ሸዋ  


አዜብ ታደሰ 
ሸዋዬ ለገሠ