1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኦባማ ሒሮሺማን የመጎብኘት ዕቅድ

ሐሙስ፣ ግንቦት 4 2008

አዉዳሚዉን ቦምብ በሰዎች ላይ በመጣል ዩናይትድ ስቴትስ እስካሁን ድረስ የመጀመሪያዋም፤ የመጨረሻዋም ሐገር ናት።በሥልጣን ላይ የሚገኝ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ሔሮሺማን ሲገበኝ ደግሞ ኦባማ የመጀመሪያዉ ይሆናሉ።

https://p.dw.com/p/1ImPR
ምስል U.S. Army/Hiroshima Peace Memorial Museum via Reuters

[No title]

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ ሐገራቸዉ በሁለተኛዉ የዓለም ጦርነት ማብቂያ በአዉቶሚክ ቦምብ ከደበደበቻቸዉ ሁለት የጃፓን ከተሞች አንዷን ሒሮሺማን በቅርቡ ይጎበኛሉ።የፕሬዝደንቱ ፅሕፈት ቤት እንዳስታወቀዉ ኦባማ በመጀመሪያዉ የአዉቶሚክ ቦምብ የተመታችዉን ከተማ የሚጎበኙት ሐገራቸዉ ላደረሰችዉ ጥፋት ይቅርታ ለመጠየቅ ሳይሆን የኑክሌር ጦር መሳሪያ እንዲታገድ ያነሱትን ሐሳብ ለማጠናከር ነዉ።አዉዳሚዉን ቦምብ በሰዎች ላይ በመጣል ዩናይትድ ስቴትስ እስካሁን ድረስ የመጀመሪያዋም፤ የመጨረሻዋም ሐገር ናት።በሥልጣን ላይ የሚገኝ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ሔሮሺማን ሲገበኝ ደግሞ ኦባማ የመጀመሪያዉ ይሆናሉ።የዋሽግተን ዲሲዉ ወኪላችን ናትናኤል ወልዴ ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።

ናትናኤል ወልዴ

ነጋሽ መሐመድ

አዜብ ታደሰ