1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኦልመርት ስልጣናቸውን እንደሚለቁ ማስታወቃቸው

ዓርብ፣ ሐምሌ 25 2000

በሙስና ቅሌት ብዙ ሲወቀሱና ግፊት ሲደረግባችው የቆዩት የእሥራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ኤሁድ ኦልመርት የፓርቲና የመንግሥት ሥልጣናችውን እንደሚለቁ በትናንትናው ዕለት አስታውቀዋል። ኦልመርት ሥልጣናቸውን በፊታችን መሥከረም ወር አዲስ ለሚመረጠው የካዲማ ፓርቲያችው ሊቀ-መንበር እንደሚያስረክቡ ነው የገለጹት።

https://p.dw.com/p/EoEP
ግፊት የተጠናከረባቸው የእስራኤል ጠቅላይ ሚንስትር
ግፊት የተጠናከረባቸው የእስራኤል ጠቅላይ ሚንስትርምስል picture-alliance/ dpa

የሚገመተው የአገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዚፒ ሊቭኒ ወይም የመገናኛ ሚኒስትሩ ሻውል ሞፋስ ተተኪያቸው እንደሚሆኑ ነው። የተቃዋሚው ፓርቲ ግን ከጠቅላይ ሚኒስትር ለውጥ ይልቅ በሀገሪቱ አዲስ ምርጫ መካሄዱን ነው የሚሻው።