1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኦላንድ ለፕሬዝዳንትነት ተመረጡ

ሰኞ፣ ሚያዝያ 29 2004

ትናንት ፈረንሳይ ውስጥ በተካሄደው 2 ኛ ዙር የማጣሪያ ምርጫ ሶሻሊስቱ ፍርንሷ ኦሎንድ ድል ተቀዳጅተዋል ። ከመጀመሪያው ዙር ውጤት በኋላ እንደሚያሸንፉ በሰፊው የተነገረላቸው ኦሎንድ 51.6 በመቶ የመራጭ ድምፅ አግኝተው ከ 17 ዓመት በኋላ

https://p.dw.com/p/14rPR
ተመራጩ ኦሎንድምስል dapd

ትናንት ፈረንሳይ ውስጥ በተካሄደው 2 ኛ ዙር የማጣሪያ ምርጫ ሶሻሊስቱ ፍርንሷ ኦሎንድ ድል ተቀዳጅተዋል ። ከመጀመሪያው ዙር ውጤት በኋላ እንደሚያሸንፉ በሰፊው የተነገረላቸው ኦሎንድ 51.6 በመቶ የመራጭ ድምፅ አግኝተው ከ 17 ዓመት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ፓርቲያቸውን ለሥልጣን አብቅተዋል ። የአውሮፓ የኢኮኖሚ ቀውስ ያስከተላቸው የቁጠባ አሠራር ሥራ አጥነትና የኑሮ ውድነትን የመሳሳሉት መዘዞች ፕሬዝዳንት ኒኮላ ሳርኮዚን ለሽንፈት ያበቃቸው ምክንያቶች መሆናቸው ይወሳል ። ተሰናባቹ ፕሪዝዳንት ሳርኮዚ 48.4 በመቶ ድምፅ ነው ያገኙት ። ተመራጩ ፕሬዝዳንት ፍራንሷ ኦሎንድ ከ10 ቀናት በኋላ ሥልጣኑን በይፋ ይረከባሉ ተብሎ ይጠበቃል ። ሃይማኖት ጥሩነህ ከፓሪስ ዝርዝር ዘገባ አዘጋጅታለች

ሃይማኖት ጥሩነህ

ሂሩት መለሰ

ሸዋዮ ለገሰ