1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኦሊምፒክና ሥነ ቴክኒክ

ረቡዕ፣ ሐምሌ 18 2004

ከነገ በስቲያ ፣ የኦሊምፒክ እስፖርት ውድድር በልዩ ሥነ ሥርዓት እንደሚጀመር ይጠበቃል። የአዲሱ ዘመን የኦሊምፒክ እስፖርት በ 1896 እንደገና ከተጀመረ ወዲህ፤ በዘመናት ሂደት ሥነ ቴክኒክ ለተለያዩ የእስፖርት ዓይነቶችና ውድድሮች ምን ውጤት ፣

https://p.dw.com/p/15ecx
ምስል AP

 አስመዝግቦ፤፣ ምን ዓይነት አስተዋጽዖስ  አድርጎ ይሆን?! ሥነ ቅመማው (ኬምስትሪው) በአትሌቶች አመጋገብ፤ ፊዚክሱ፤ በማንኛውም የውድድር ዓይነት ፤ ፍጥነትን ፤ ከፍታን  የአየር ግፊትን  ፣ የስበት ኃይልን ሲዳስስ፤ ሥነ ህይወቱ፤ የስነ ልቡና ይዞታን፤ የደም ዝውውርን ፣ እስትንፋስን፣ ሙቀትን  ብርድን፣ በአጠቃላይ  የጤንነት ይዞታን ሊመለከት ይችላል። 

Äthiopien Kenenisa Bekele
ምስል picture-alliance/dpa

«ዲስከስ» ውርወራ፤ መዋኛ ኩሬን በፍጥነት ሰንጥቆ የመሻገሩ  ዘዴ ፣ ሽምጥ ሩጫው፣ የአጭርና ረጅም ርቀት አሯሯጥ፣ የምድርና የአየር ዝላይ፣ ለቅርጫትና መረብ ኳስ፤ ለቴኒስ፤ ለእነዚህና ለመሳሰሉት  ሁሉ የእስፖርት ዓይነቶችም ፣ በተለያየ  የአየር ጠባይ  ተስማሚ የሆኑ የእስፖርት መሣሪያዎችንና መጫሚያዎችን የማሰናዳቱን ፣ ውጤትም የማስመዝገቡን  ብልሃት፤ ይህ ሁሉ ፣ ሳይንስን ፤ ሥነ ቴክኒክን፣ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ማጣቀሱ ያለ ጉዳይ ነው።  እስፖርት፤  በተለይ ም  የውድድር እስፖርት፤ ሂሳብንም ፤ ሳይንስንም መሠረት ያደርጋል።

Ob Puma oder Lilie....

ዝነኛው ዓለም አቀፍ አትሌት ፤ ኃይሌ  ገ/ሥላሴ፣ አንድ ጊዜ ለራዲዮ ጣቢያችን፣ ሩጫ እንዲሁ ሩጫ አይደለም ፤ ስሌት ያለበት  ሂሳብ ነው፤ ያለውን ያስታውሷል። ሥነ ቴክኒክ ለእስፖርት ስለሚያበረክተው ድርሻ፣ በለንደን ኑዋሪ የሆነው የቅርጫት ኳስ ተጫዋችና አሠልጣኝ  ሳሙኤል ብርሃኑ--

ከተለያዩ ፣ ለእስፖርት ከሚጠቅሙ መሳሪያዎች ባሻገር በቀጥታ አትሌቶች የሚገለገሉባቸው ጫማዎች ፣ ለሩጫም  ሆነ ለአግር ኳስ፣ ቅርቻት ኳስ፣ መረብ ኳስ፣ ቴኒስና ለመሳሰለው በየጊዜው እየተሻሻሉ መሠራታቸው አልቀረም። የአካል ጉዳተኞች ለሆኑ እስፖርተኞች ይጠቅማሉ የሚባሉ ልዩ - ልዩ የጫማ ዓይነቶችም ይቀርባሉ። በጀርመን ሀገር ፣ኑዑረንበርግ ከተማ አቅራቢያ የሚገኘው የአዲዳስ ኩባንያ፣ በበኩሉ ለሽምጥ ሯጮች የሚበጅ 99 ግራም ብቻ የሚመዝን ጫማ ሠርቼአለሁ ማለቱን ሰምተናል፤  በጋዜጣም አንብበናል። ከእግር ጣቶች እስከ ተረከዝና ቁርጭምጭሚት ፣ ጉዳት የማያስከትል የማያቆስል፤ ፍጥነትንም የማይገታ ፤ ፍጹም ወደር የሌለው ጫማ፤ እውን ቀርቦ ይሆን?! ስለ እስፖርት ጫማ፣ ፈጣን እንቅሥቃሤ የሚደረግበት የቅርጫት ኳስ ተጫዋችና አሠልጣኝ ሳሙኤል እንዲህ ይላል።

Behindertensport
ምስል picture-alliance/dpa
Bildergalerie Brasilianische Sportler Olympischen Sommerspiele 2012
ምስል AP

ተክሌ የኋላ 

አርያም ተክሌ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ