እየተበራከተ የመጣዉ አስከፊ የጭነት መኪና አደጋ
ሰኞ፣ የካቲት 30 2007ማስታወቂያ
አንድ ኢትዮጵያዊ የኤሌክትሮ መካኒካል ባለሞያ እንደሚሉት ችግሩ ከተሽከርካሪዉ ጉድለት ሳይሆን ችግሩ እየተከሰተ ያለዉ በመንጃ ፈቃድ አሰጣጥ ጉድለት ሳይሆን አልቀረም። የፊደራል የትራንስፖርት ባለሥልጣን በበኩሉ የመንጃ ፈቃድ አሰጣጥ ችግር የሚለዉ መላምት ትክክል አይደለም። ይሁን እንጂ አሽከርካሪዎቹ የትራፊክ ሕግን አክብሮ ባለማሽከርከርና መኪናዉን ከአቅም በላይ ጭነት በማሸከም ነዉ፤ ሲሉ አስተያየታቸዉን ሰጥተዋል። እየተበራከተ የመጣዉን የመኪና አደጋ ችግር መንስኤዉን ለማወቅ አንድ የአጥኚ ቡድን ተቋቁሞ የችግሩን መንስኤ በማፈላለግ ላይ መሆኑም ተገልፆአል።
ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር
አዜብ ታደሰ
አርያም ተክሌ