እንቁጣጣሽ-የ2007 ልዩ ዝግጅት
ሐሙስ፣ መስከረም 1 2007ማስታወቂያ
የአዉዳመቱን ዝግጅት ከአዲስ አበባ የፓትርያርኩን መልክት ይዘን፤ በኢትዮጵያ አሮጌዉን ዓመትን ጥሎ ወደ አዲሱ ዓመት የተዛወረዉ የመብራት መጥፋትና መቆራረጥ ችግር፤ ክብረ በዓሉ ላይ ያጣለዉን አሉታዊ ገፅታ ዳሰን፤ በአዉሮጳና ና በሰሜን አሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን አዲስ ዓመትን እንዴት እንተቀበሉት? አዲስ ዓመትን በሃገራቸው በድምቀት ያከበሩ ኢትዮጵያውያን ከሃገር ሲወጡ ከትዝታቸው ጋር ነው።ለስራ ወይም ለትምህርት በተጓዙባቸው ሃገራት በዓልን በቀደመው ልክ ማክበር አይሆንላቸውም። የአዲስ ዓመት በዓል ትዝታ ምን ይመስላል? ከአዲስ አበባ ከለንደን ከጀርመን እና ከዩኤስ አሜሪካ ያዘጋጀናቸዉን የአዉዳመት ልዮዝግጅት የድምፅ ማዕቀፉን በመጫን ይከታተሉ!
አዜብ ታደሰ
ተክሌ የኋላ