እናት ባንክ
ሰኞ፣ መጋቢት 16 2005ማስታወቂያ
260 ሚሊዮን ብር መንቀሳቀሻ ወረት የሚኖረውን አዲሱን ባንክ የተለየ የሚያደርጉት አንዳንድ ነጥቦች አሉ። በቅርቡ ሥራውን የጀመረው አዲሱ ባንክ 64 በመቶ የአክሲዮን ባለድርሻዎች ሴቶች ናቸው። የባንኩ የመጀመሪያ ቅርንጫፍ «ጣይቱ» የሚል ሥያሜ የተሰጠው ሲሆን፤ ንግሥተ ሳባና አበበች ጎበና የሚሰኙ ቅርንጫፎችም ፣ ባንኩ የሚከፍት መሆኑን አስታውቋል። ቁጥራቸው እየጨመረ የሚሄደው የባንኩ ቅርንጫፎች፤ በኢትዮጵያ ታሪክ አወንታዊ አስተዋጽዖ ባደረጉ ሴቶች ሥም እንደሚሰየሙም ተመልክቷል። ሴቶች ላቅ ያለ የአመራር ኀላፊነት የተሸከሙበት ፣ ከፍ ያለ የሥራ ድርሻም የሚያበረክቱበት ባንክ መክፈት ለምን አስፈለገ?
ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር
ተክሌ የኋላ
ነጋሽ መሀመድ