1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

«እሽቲፍቱንግ ዞላር ኢነርጊ» በኢትዮጵያ፣

ረቡዕ፣ ሚያዝያ 30 2005

ዋና ማዕከሉ ፤ ጀርመን ውስጥ፤ በባደን ቩርተምበርግ ፌደራል ክፍለ- ሀገር፤ ፍራይቡርግ አቅራቢያ ፣ Merzhausen በተባለችው ንዑስ ከተማ ነው። በእስዊትስዘርላንድ Zürich ውስጥም ቅርንጫፍ አለው። በአዳጊ አገሮች፤ ኢትዮጵያ ፤ ኬንያና

https://p.dw.com/p/18UE4
ምስል Stiftung Solarenergie

ፊሊፒንስ ውስጥ በዘረጋቸው ፕሮጀክቶች ፣ ዘንድሮም Energy Globe Award የተሰኘውን ሽልማት ማሸነፉ የተነገረ ሲሆን፤ ሽልማቱን ፣ ግንቦት 28 ቀን 2005 ፣ ማለት በተባበሩት መንግሥታት የዓለም -የተፈጥሮ አካባቢ መታሰቢያ ዕለት ፣ በይፋ ይቀበላል ፦

«እሽቲፍቲቱንግ ዞላር ኢነርጊ» የተሰኘው በፀሐይ ኃይል ኤሌክትሪክ አመንጪ መሣሪያ አምራቹ ድርጅት ኢትዮጵያ ውስጥ የሚያከናውነው ተግባር--

Äthiopien Solar
ምስል Stiftung Solarenergie

የፀሐይ ኃይል ምንጭ ድርጅት የተሰኘው የጀርመን ተቋም !(እሽቲፍቱንግ ሶላር ኤነርጊ) (ሶላር ኢነርጂ ፋውንዴሽን) ። ይኸው «እሽቲፍቱንግ ዞላር ኢነርጊ» ከ 150 አገሮች የተውጣጡ 1,000 ያህል ፕሮጀክቶች ባደረጉት ውድድር ነው በአሸናፊነት የተመረጠው።

ለሁለተኛ ጊዜ ፤ ለዚህ ሙገሣና ውደሳ ብሎም ለሽልማት ያበቃው ምንድን ነው? የዚህን ድርጅት የቦርድ አማካሪዎች ፕሬዚዳንት ዶ/ር Harald Schützeichel ን አነጋግሬአቸው ነበር።

«ኢትዮጵያ ውስጥ፣ እ ጎ አ ከ 2004 ዓ ም አንስቶ በዚያ እንደተሠማራን እንገኛለን። በዚያም በገጠር ፤ በፀሐይ ኃይል የኤሌክትሪክ አገልግሎት የሚስፋፋበትን ተግባር ነው የምናከናውነው። መብራት እናስገባለን፤ ይህም ለአጅ(ተንቀሳቃሽ ስልኮች ኃይል መሙያ፣ ለቴሌቭዥን ፣ ለማቀዝቀዣ መሣሪያ፣ ለውሃ መሳቢያና ለመሳሰለ አገልግሎት እንዲሰጥ ይደረጋል። »

Äthiopien Solar
ምስል Stiftung Solarenergie

የኤሌክትሪክ አገልግሎት ማግኘት፣ ከዚህ ጋር የሚያያዙ ጠቃሚና ተፈላጊ ጉዳዮችን ለማከናወንም ይረዳል ። 22,000 የፀሐይ ኃይል አጥማጅ መሣሪያዎች፣ በመኖሪያ ቤቶች በትምህርት ቤቶች፤ በተለያዩ ጣቢያዎችና ተግባ ራዊ ሆኗል። 35 የጤና ጣቢያዎች፤ በፀሐይ ኃይል የሚሠሩ ማቀዝቀዛዎች አግኝተዋል። ይህም መድኃኒት ሳይበላሽ ማስቀመጥ እንዲቻላቸው ከ 150 በላይ የሚሆኑ ትምህርት ቤቶች ማታ -ማታ ለማስተማር እንዲችሉ የኤሌክትሪክ መብራት ገብቶላቸዋል። በፀሐይ ኃይል የኤሌክትሪክ አገልግሎት ማግኘት ስለሚቻልበት ሁኔታ በሚሰጠው ማሰልጠኛ ትምህርት 450 ወጣቶች ይሳተፋሉ። ዶ/ር ሹዑትዝአይሼል በተጨማሪ ሲያብራሩ---

Äthiopien Solar
Äthiopien Solarምስል Stiftung Solarenergie

«በዚህ ረገድ በአንድ በኩል ትምህርትን ለማሻሻል ይቻላል። የጤንነት ይዞታንም ይበልጥ ለመጠበቅ እንደሚበጅ አያጠራጥርም። ለምሳሌ ያህል፤ የኩራዝ መብራት ለጤና ተስማማሚ እንዳልሆነ የታወቀ ነው። እንዲሁም በዚህ የኤሌክትሪክ መብራትና ኃይል ሳቢያ በገጠር ልማት ሊስፋፋ እንደሚችልም ነው መንገዱን የምናሳየው። »

እንዴት ነው ይህ በበጎ አድራጎት የሚከናወን ፣ የሥነ ቴክኒክ ዝውውር ነው ፣ ወይስ የገጠሩን ህዝብ ታስከፍሉታላችሁ ማለት ነው?

«ይህን እንደ አንድ የበጎ አድራጎት ድርጅት ነው የምናከናውነው፤ ነገር ግን፤ ከፀሐይ ፤ የኤሌክትሪክ ኃይል የሚጠራቀመውን አውታር ፤ በነጻ አይደለም የምንዘረጋው። እንሸጣለን። ዞሮ - ዞሮ፣ የበጎ አድራጎት ተግባር የምንለው፣ ከማያስፈልግበት ደረጃ እንዲደርስ ነው ፍላጎታችን።

በኢትዮጵያ ፤ በፀሐይ ኃይል የሚሠሩ አውታሮችን የሚጠግኑ ኢትዮጵያውያን ቴክኒሻኖች ያስፈልጋሉ። በመጠገን፤ አውታሮችን በመዘርጋትና በመሳሰለው ሙያ ተሠማርተው ኑሮአቸውን መምራት ስለሚኖርባቸው፤

በአነስተኛ ወለድ ገንዘብ በማበደር፤ በፀሐይ ኃይል ኤሌክትሪክ አመንጪ አውታሮችን እንዲገዙ እናደርጋለን። በመሃሉም፤ ከ 60 በላይ ቴክኒሻኖችን አሠልጥነናል። » (ይቀጥላል)

ተክሌ የኋላ

ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ