1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

እስር ላይ የሚገኙ የተቃዋሚ ፖለቲካ አመራሮች ችሎት

ሰኞ፣ የካቲት 7 2008

የሽብርተኝነት ክስ ተመስርቶባቸው በፌደራል ክፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት መከላከል ሳያስፈልጋቸው በነፃ እንዲሰናበቱ ከተበየነላቸው በኋላ አቃቤ ሕግ ይግባኝ ጠይቆባቸው ጉዳያቸው በጠቅላይ ፍርድ ቤት እየታየ የሚገኙት የሰማያዊ፣ የአንድነትና የአረና ፓርቲ አመራሮች ለምን ሊፈቱ እንዳልቻሉ አጥጋቢ መልስ አለመሰጠቱ ተመለከተ።

https://p.dw.com/p/1Hvlh
Symbolbild Justitia Justizia
ምስል picture-alliance/dpa

[No title]

አምስቱ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች አቶ የሺዋስ አሰፋ፣ አቶ አብርሃ ደስታ፣ አቶ ሀብታሙ አያሌው፣ አቶ ዳንኤል ሽበሺና አቶ አብርሃም ሰለሞን ሲሆኑ ተከሳሾቹ ዛሬ በእስር ላይ ሆነዉ በከፍተኛ ፍርድ ቤት ቀጠሮ ላይ መገኘታቸዉ ታዉቋል። የአዲስ አበባዉ ወኪላችን የተከሳሾቹን ጠበቃ አቶ አመሃ መኮንንን አነጋግሮ ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል።


ጌታቸዉ ተድላ ኃ/ጊዮርጊስ


አዜብ ታደሰ
ኂሩት መለሰ