የእስራኤል ርምጃ ኤርትራውያን ስደተኞችን ይመለከታል
ማክሰኞ፣ ኅዳር 12 2010ማስታወቂያ
ከእስራኤል የሚባረሩት ተገን ፈላጊዎች ያለፈቃዳቸው እንደሆነ በዘገባዎች ተገልጿል። ከጎርጎሮሳዊው 2000 የመጀመሪያ አመታት ጀምሪሮ ኤርትራውያን እና ሱዳናውያን በግብፅ በኩል ወደ እስራኤል ቢገቡም በሀገሪቱ ግን ተቀባይነት አላገኙም። ስደተኞቹ በእስራኤላውያን ዘንድ "ሰርጎ ገቦች" የሚል ስም እንደተሰጣቸው ዘገባዎች አመልክተዋል። ሐሬትዝ የተባለው የእስራኤል ዕለታዊ ጋዜጣ ኔታንያሁ ተገን ጠያቂዎችን ወደ ሩዋንዳ ለመላክ ስምምነት ደርሰዋል ሲል ባለፈው ወር ዘግቦ ነበር። እየሩሳሌም ከሚገኘው ዘጋቢያችን ዜናነህ መኮንን ጋር የተደረገውን ቃለምልልስ የድምጽ ማዕቀፉን ተጭነው ያድምጡ።
ዜናነህ መኮንን
ተስፋለም ወልደየስ
አርያም ተክሌ