እስራኤል የደቡብ ሱዳን ስደተኞችን ማባረሯ
ሰኞ፣ ሰኔ 11 2004ማስታወቂያ
ከእስራኤል የተባረሩት የመጀመሪያዎቹ የደቡብ ሱዳን ስደተኞች ዛሬ ደቡብ ሱዳን መዲና ጁባ ገብተዋል ። እስራኤል መንግስት እንዳስታወቀው የተቀሩትን የደቡብ ሱዳን ስደተኞች ወደ ሃገራቸው የማጓጓዙ ሥራ በመጪዎቹ ሳምንታትም ይቀጥላል ። የእስራኤል የሃገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ኢሊ ይሻል ስደተኞቹ ሲሸኙ በአውሮፓላን ማረፊያ ተገኝተው ነበር ሚኒስትሩ ከዚህ ቀደም በሰጡት መግለጫ በመጀመሪያ የደቡብ ሱዳንና የኮት ዲቮር ስደተኞችን ከዚያም የ ኤርትራና የሱዳን ስደተኞችን ከእስራኤል ጠራርገው እንደሚያስወጡ ተናግረው ነበር ። የእስራኤል ሃይፋውን ወኪላችንን ግርማው አሻግሬን በስልክ አነጋግሪዋለሁ ።
ግርማው አሻግሬ
ሂሩት መለሰ
አርያም ተክሌ