1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

እስራኤልና አፍሪቃዉያን ስደተኞች

ሰኞ፣ ሐምሌ 19 2002

በእስራኤል የሚገኙ የኤርትራና ሱዳን ስደተኞች ከእስራኤላዉያን የመኖሪያ ክልሎች ለቀዉ ወደአገራቸዉ አለያም የአገሪቱ መንግስት ለስደተኞች የመኖሪያ ክልል ሰርቶ እንዲያሰፍራቸዉ የቴልአቪቭ ኗሪዎች እየጠየቁ ነዉ።

https://p.dw.com/p/OUqK
ምስል AP

የከተማዋ ኗሪዎች ኤርትራዉያንም ሆኑ ሱዳናዉያን ስደተኞች ለሥራ ፍለጋ አገራችን የገቡ ናቸዉ የሚል ስሜት ያንፀባርቃሉ። ስደተኞቹ ቁርማርተኛ፤ ሰካራም፤ ዘራፊ፤ እንዲሁም አደገኛ እፅ አዘዋዋሪ ናቸዉ ብለዉም ይተቻሉ። በእስራኤል የጥምሩ መንግስት አባል የሻዝ ፓርቲ በኅብረተሰቡ ዉስጥ ተሰራጭተዉ የሚገኙ አፍሪቃዉያን ስደተኞችን በሚመለከት ለቀረበዉ ጥያቄ ትክክለኛ መፍትሄ ካልሰጡ ጥምር መንግስቱን ለቆ እንደሚወጣ ለጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ናታንያሁ ማሳሰቢያዉን አቅርቧል።

ዜናነህ መኮንን፤

ሸዋዬ ለገሠ

ሂሩት መለሰ