1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኤች አይቪና የማኅበረሰቡ ግንዛቤ

ማክሰኞ፣ ታኅሣሥ 13 2002

ኢትዮጵያ በኤች አቪ ቫይረስ ከፍተኛ ጉዳት ከደረሰባቸዉ የአፍሪቃ አገራት መካከል አንዷ ናት።

https://p.dw.com/p/LAsr
ምስል picture-alliance/ dpa

ስለቫይረሱ ግንዛቤ ከተገኘበት ወቅት አንስቶ በርካታ ማኅበረሰቡን ሊያስተምሩ የሚችሉ ዝግጅቶች ይከናወናሉ። የመገናኛ ብዙሃኑም ሰፊ ቦታ ሰጥተዉ ሲዘግቡበት ይስተዋላል። ከምንም በላይ ቫይረሱ በደማቸዉ የሚገኝ ወገኖች በሌላዉ ሊከተል የሚችለዉን መገለልና መድሎ ችለዉ ቫይረሱ በጤናቸዉ ላይ የሚያደርሰዉን ጉዳት በግልፅ ሲያስተምሩ ቆይተዋል፤ ዛሬም እያስተማሩ ነዉ። ከቫይረሱ ራስን የመከላከሉ ርምጃ መወሰድ ያለበት በእያንዳንዱ ግለሰብ በመሆኑ የሚሆነዉ ሲሆን እየታየ ነዉ። ዛሬም የኤች አይቪ ቫይረስ ስርጭት አልተገታም።

ሸዋዬ ለገሠ

ተክሌ የኋላ