ኤርትራውያን ያስተባበሩት ተቃውሞ
ሐሙስ፣ ግንቦት 15 2005ማስታወቂያ
በስደት ላይ የሚገኙ ኤርትራውያን ፣ ሃገር ቤት ያሉ ኤርትራውያንን በማበረታታት በኤርትራ መንግሥት ላይ ያላቸውን ተቃውሞ በጋራ መግለፅ የጀመሩበትን አዲስ መንገድ በማስፋፋት ላይ መሆናቸውን አስታወቁ ። እነዚሁ የኤርትራ ህገ መንግሥት ተግባራዊ ሆኖ ምርጫ እንዲጠራ ና የፖለቲካ እሥረኞች እንዲፈቱ የሚጠይቁ ኤርትራውያን እንደ ጎርጎሮሳውያን አቆጣጠር ከ2011 መጨረሻ አንስቶከውጭ ወደ ሃገር ውስጥ ጥሬያቸውን በስልክ እያስተላለፉ ነው ። ሃሳባቸውን በነፃነት መግለፅ ያልቻሉ ኤርትራውያን አርብ ምሽት ከቤታቸው ባለመውጣት ተቃውሞ እንዲያደርጉ በማበረታት ላይ መሆናቸውንም የለንደንዋ ወኪላችን ሃና ደምሴ ዘግባለች ።
ሃና ደምሴ
ሂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ