ኤርትራዊዉ አሜሪካዊ የተፈፀመበት ግፍ
ማክሰኞ፣ ሚያዝያ 16 2004ማስታወቂያ
አቡዳቢ ዉስጥ ታስሮ መገረፍ፥ መሰቃየት፥ እና ከተለቀቀ በሕዋላ ወደ አሜሪካ እንዳይገባ መከልከሉን አስታወቀ።ቶማስና ጠበቃዉ እንደሚሉት ቶማስ ከአንድ መቶ ቀናት በላይ ታስሮ ሲለቀቅ የተመሠረተበት ክስ አልነበረም።እስር ቤት በነበረበት ወቅት ደግሞ የአሜሪካ ማዕከላዊ ቢሮ (FBI) ባልደረቦች ወይም ተባባሪዎች ናቸዉ ብለዉ የሚጠረጥሯቸዉ ሰዎች ይገርፉት፥ ያሰቃዩት እና ለFBI እንዲሰልል ያስፈራሩት ነበር።የአሜሪካ እስላማዊ ምክር ቤት ቃል አቀባይ ኢብራሒም ሑፐር እንደሚሉት በቶማስ ላይ የተፈፀመዉ አይነት ግፍ በብዙ አሜሪካዉያን ሙስሊሞች ላይ በተደጋጋሚ እየተፈፀመ ነዉ።
አበበ ፈለቀ
ነጋሽ መሀመድ
አርያም ተክሌ