1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኤርትራዉያን ስደተኛ እና እስራኤላዉያኑ ወንጀለኞች

ሰኞ፣ መስከረም 14 2005

አራት እስራኤላዉያን እዚያ ከሚኖር አንድ ኤርትራዊ ስደተኛ ዘገባዉ አሳፋሪ ባለዉ መንገድ 13 ሺህ ዶላር ለማስከፈል መሞከራቸዉ ተገለጸ።

https://p.dw.com/p/16DT9
ምስል DW/Al Farra

አራት እስራኤላዉያን እዚያ ከሚኖር አንድ ኤርትራዊ ስደተኛ ዘገባዉ አሳፋሪ ባለዉ መንገድ 13 ሺህ ዶላር ለማስከፈል መሞከራቸዉ ተገለጸ። ከአራቱ መካከል ሶስቱ አይሁድ እስራኤላዉያን መሆናቸዉ ሲጠቀስ በእስራኤል ነዋሪ ከሆነዉ ኤርትራዊ ስደተኛ የተጠቀሰዉን ያህል ገንዘብ ካላመጣህ ሲና በረሃ ታግቶ የሚገኘዉ ዘመድህ ህይወት ያልፋል ሲሉ ማስፈራራታቸዉን የፈረንሳዩ ዜና ወኪል አዣንስ ፍራንስ ዘግቧል። አሁን በደረሰዉ ዜና መሰረት ደግሞ በዚሁ ወንጀል ሌሎች ሁለት እስራኤላዉያን መያዛቸዉ ተመልክቶአል። በእስራኤል ሃይፋ የሚገ ኘዉን ወኪላችንን ግርማዉ አሻግሬን ሁኔታዉ ምን እንደሚመስል እዚህ ስቱዲዮ ከመግባቴ በፊት ጠይቄዉ ነበር መልስ በመስጠት ይጀምራል።

ግርማዉ አሻግሪ

አዜብ ታደሰ

ሸዋዬ ለገሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ