1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኤርትራዉያን ማይ አይኒ የስደተኞች መጠለያ

ዓርብ፣ ሰኔ 15 2004

በየዓመቱ በጎርጎሮሳዊዉ የዘመን ቀመር ሰኔ 20 ቀን የዓለም የስደተኞች ቀን ተብሎ ይታሰባል። ከትናንት በስተያ የታሰበዉ የዘንድሮዉ የዓለም የስደተኞች ቀን፤ ከየትዉልድ ሀገራቸዉ በሚገጥማቸዉ ክስ፤ ግጭትና ጥቃት ስጋት ምክንያት ትዉልድ

https://p.dw.com/p/15Jxi

ሀገራቸዉን ትተዉ ለተሰደዱ ሴቶችና ወንዶች እንዲሁም ህፃናት ላሳዩት ድፍረት፤ ጥንካሬ እና ቆራጥነት የመንግስታቱ ድርጅት ባዘጋጀዉ ዝግጅት ክብር ለግሷል።  የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን UNHCR ኢትዮጵያ ዉስጥ ካለዉ መንግስታዊ ተባባሪዉ ጋ በመሆን በሰሜን ኢትዮጵያ ትግራዊ የሚገኘዉን የማይ አይኒን የስደተኞች መጠለያ አስጎበኘ። በስፍራዉ የሚገኘዉን ለስደተኞች የተቋቋመዉን አዲስ ትምህርት ቤትም አስመርቋል። ወደማይ አይኒ የስደተኞች መጠለያ አብሮ የተጓዘዉ የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ጌታቸዉ ተድላ ኃይለጊዮርጊስ ቀጣዩን ዘገባ ጠናቅሯል።

ጌታቸዉ ተድላ ኃይለጊዮርጊስ

ሸዋዬ ለገሠ

አርያም ተክሌ