1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢጣልያ ስደተኞችን ለማስተናገድ የአዉሮጳ ሀገራትን እርዳታ መጠየቋ

ሰኞ፣ ግንቦት 11 2006

ከሰሜናዊ አፍሪቃ ሜዲትራንዬን ባህርን አቋርጠዉ ወደ ሀገርዋ የሚገቡባት ኢጣልያ ፤ ስደተኞችን ለማስተናገድ ከሌሎች አዉሮጳዉያን ሀገራት ርዳታ ይደረግልኝ ሥትል ጠየቀች። ወደ ኢጣልያ የሚገቡት የጀልባ ሥደተኞች ቁጥር እየጨመረ መሄዱ ተመልክቶአል።

https://p.dw.com/p/1C2aa
Flüchtlinge in Italien März 2014
ምስል picture-alliance/AP Photo/Italian Coast guard

ባለፈዉ ሳምንት አንድ ከሊቢያ የባህር ዳርቻ ሥደተኞችን የጫነች ጀልባ ወደ ኢጣልያ በመቅዘፍ ላይ ሳለ ለአደጋ ተጋልጦ 17 የጀልባዉ ተሳፋሪዎች ባህር ዉስጥ መስመጣቸዉና፤ 206 ሰዎች ደግሞ በኢጣልያ የባህር ኃይል ከአደጋ መታደጋቸዉ ተመልክቶአል። በተመሳሳይ ባለፈዉ ሳምንት ሊቢያ ባህር ዳርቻ 40 የጀልባ ስደተኞች ባህር ዉስጥ መስመጣቸዉ ተዘግቦአል። እንድያም ሆኖ በርካታ ስደተኞች አሁንም ባህር እያቋረጡ ወደ ጣልያን በመግባት ላይ መሆናቸዉ ነዉ የተነገረዉ። ዝርዝሩን የኢጣልያ ሮማዉ ዘጋቢያችን ተክለእዝጊ ገብረየሱስ አድርሶናል።

ተክለዝጊ ገ/ እግዚአብሄር

አዜብ ታደሰ

አርያም ተክሌ