ኢንጅነር ገበያው እምቢአለ
ማክሰኞ፣ የካቲት 1 2008የዚህ ግዙፍ አውሮፕላን የተለያዩ አካላት የዲዛይን ስራ በተለየ ትኩረትና ጥንቃቄ እንዲሁም ክትትል ነው የሚከናወነው ።ኤርባስ የስፓኝ የፈረንሳይ የእንግሊዝና የጀርመን የጋራ ኩባንያ ነው ።ኢንጅነር ገበያው እንደሚሉት ከዓለም በግዙፍነቱ የመጀመሪያውን ደረጃ የሚይዘው የዚህ ኩባንያ ምርት የ ኤ-380 አውሮፕላን የተለያዩ አካላት ዲዛይን የሚደረጉትና የሚመረቱትም በነዚህ አራት ሃገራት ውስጥ ነው ።በሚሰሩበት በሃምቡርጉ የኤርባስ የኢንጅነሪንግ ና ዲዛይን መስሪያ ቤት የኢንጅነር ገበያውና የባልደረቦቻቸው የስራ ድርሻ ምን ይሆን ?ኢንጅነር ገበያውተወልደው ያደጉት የአንደኛ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውንም የተከታተሉት ሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ በሚገኘው በቻግኒ ከተማ ነው ። የልጅነት ምኞታቸው ኮሌጅ ወይ ዩኒቨርስቲ መግባት ነበር ። ይህ ምኞታቸው እውን ሆኖ በባህርዳሩ የፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለ3 ዓመት አግሮ መካኒክስ ተምረው በከፍተኛ ውጤት በማጠናቀቃቸው እዚያው ኮሌጅ ውስጥ በመምህርነት ማገልገል ጀመሩ ። 2 አመት ካስተማሩ በኋላ ደግሞ የነፃ ትምህርት እድል አግኝተው ጀርመን መጡ ። በበርሊኑ የሁምቦልት ዩኒቨርስቲ መካኒካል ኢንጅነሪንግ ካጠኑ በኋላ በደቡብ ጀርመንዋ ሽቱትጋርት በሚገኝ የኢንጅነሪንግ መሥሪያ ቤት ለሁለት ዓመት ሠርተዋል ።ጀርመን ሲኖሩ ከጀመሩ 27 ተኛ አመታቸውን ያስቆጠሩት ኢንጅነር ገበያው ከተወሰኑ ዓመታት ወዲህ በጀርመን ከአንዳንድ የህብረተሰብ ክፍሎች በኩል የሚንጸባረቀውን የውጭ ዜጎች ጥላቻ የደካሞች አመለካከት ይሉታል ። የውጭ ዜጋም የበኩሉን አስተዋፅኦ በሚያደርግባት በጀርመን ተቀባይነት የሌለው ሲሉም ይቃወሙታል ።ባለትዳርንና የሁለት ልጆች አባት ኢንጅነር ገበያው አሁን ከደረሱበት የሙያ ደረጃ በተጨማሪ ሌላም ምኞት አላቸው ።
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሰ