1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢንዶኔዥያዊቷ የቤት ሰራተኛ የደረሰባት በደል

ማክሰኞ፣ ሰኔ 21 2003

በየአገሩ በሚከሰቱ ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ምክንያት በየአጋጣሚው ሰዎችን እንደ እቃ መጠቀሚያ የሚያደርጉ ግለሰቦችና ድርጅቶች ግንባር ቀደም ሰለባዎች ሴቶች ናቸው ።

https://p.dw.com/p/RWIO
በቤት ሠራተኝነት ወደ ውጭ አገር የሚሄዱ ኢንዶኔዥያውያን በስልጠና ላይምስል picture alliance/ANN/The Jakarta Post

በአሁኑ ሰዓት ከቀያቸው ርቀው በየሃገሩ በቤት ሰራተኝነት ለጉልበት ብዝበዛ የተዳረጉ ፣ ለጤና እክል የተጋለጡ ችግሩም ሲከፋም ህይወታቸውን እሰከማጣት የደረሱ እና ሳይወዱ በግዳጅ በዝሙት የተሰማሩም ሴቶች ቁጥር ከፍተኛ ነው ። ሴቶች ለዚህን መሰሉ ችግር በስፋት ከተጋለጡባቸው አካባቢዎች ውስጥ መካከለኛው ምሥራቅ በግንባር ቀደምትነት ይጠቀሳል ። ወደ አረብ ሃገራት በህጋዊም ይሁን በህገ ወጥ መንገድ የሄዱ እህቶች ኢትዮጵያውያን ጨምሮ ለነዚህ ችግሮች እንደሚዳረጉ በተደጋጋሚ የተነገረ ጉዳይ ነው ። ችግሩ ግን በነዚህ ሃገራት ብቻ የተወሰነ አለመሆኑን አልፎ አልፎ በአውሮፓ እና በአሜሪካንም ደረሱ ከሚባሉ ተመሳሳይ ክስተቶች መረዳት ይቻላል ። ለዚህም ጀርመን መዲና በርሊን በአንድ ዲፕሎማት ቤት ውስጥ በሰራተኝነት ስታገለግል በነበረች ኢንዶኔዥያዊት ላይ የተፈፀመው በደል አንድ ምሳሌ ሆኖ ቀርቧል።

ሂሩት መለሰ

ነጋሽ መሐመድ