ኢትዮጽያ የኤሌትሪክ ሃይል ይዞታና የተያዘዉ እቅድ
ዓርብ፣ ጥር 7 2002ማስታወቂያ
ሁለት ቀናት በፊት ደግሞ የግልገል ግቤ የሃይል ማመንጫ ተጠናቆ መመረቁም ይታወቃል። በመቀጠል ከሁለት ወራት በኻላ ከበለስ የሃይል ማመንጫ አራት መቶ ሜጋ ዋት ሃይል ማመንጨት እንደሚቻልም ተገልጾአል። የሃይል ምንጭ ግድቦች ተሰርተዉ መጠናቀቅ በአገሪቱ ተፈጥሮ የነበረዉን የሃይል እጥረት በማማሏት ኢኮነሚዉን እንደሚያነቃቃዉ ሲገለጽ በሌላ በኩል ምርጫዉ በሚደረግበት አመት የግድቡ መመረቅ ገዥዉ ፓርቲ ለምርጫ ቅስቀሳ ሊጠቀምበት ፈልጎ ነዉ ተብሏል። አገሪቷ የሃይል ምንጯን ከራስዋ አልፋ ለጎረቤት አገሮች ብሎም ለአዉሮጻ ለመሸጥ ማቀድዋ ደግሞ በመነገር ላይ ነዉ። ይህ ሁሉ ሊሆን የሚችል ነዉን? ወኪላችን ታደሰ እንግዳዉ በኢትዮጽያ የኢሌትሪክ ሃይል ዙርያ በኢትዮጽያ ሳምንታዊ የኢኮነሚ ጋዜጣ አዘጋጅ እና ባለቤትን አነጋግሮ ይህን አጠናቅሮልናል።
ታደሰ እንግዳዉ፣ አዜብ ታደሰ
አርያም ተክሌ
ታደሰ እንግዳዉ፣ አዜብ ታደሰ
አርያም ተክሌ