1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢትዮጵያ ጋዜጠኞችን እንድትፈታ አሜሪካ አሳሰበች

ሐሙስ፣ ታኅሣሥ 21 2008

ኢትዮጵያ ከሰሞኑ በቁጥጥር ስር ያዋለቻቸውን ጋዜጠኞችና ግለሰቦች በአስቸኳይ እንድትፈታ ዩናይትድ ስቴትስ ጠየቀች። የዩናይትድ ስቴትስ የብሄራዊ ደህንነት ካውንስል ቃል አቀባይ ኔድ ፕሪስ ሀገራቸው የኢትዮጵውያኑ ጋዜጠኞች እስር «እንዳሳሰባት» ተናግረዋል።

https://p.dw.com/p/1HWct
Äthiopien Barack Obama Hailemariam Desalegn PK
ምስል Getty Images/AFP/S. Loeb

[No title]

የዩናይትድ ስቴትስ የብሄራዊ ደህንነት ካውንስል ቃል አቀባይ ኔድ ፕሪስ ረቡዕ ታኅሣሥ 20 ቀን፣ 2008 ዓ.ም. ትናንት ማምሻውን በጽሑፍ ባወጡት መግለጫ እንዳስታወቁት የኢትዮጵያ መንግስት ፀረ-ሽብር ሕግን ዜጎቹን ለማፈን፣ የጋዜጠኞችንና የኢንተርኔት ጸሓፍትን ሥራ ለመገደብ ከመጠቀም እንዲቆጠብ አሳስበዋል። ናትናኤል ወልዴ ከዋሽንግተንዲሲ ተጨማሪ ዘገባ ልኮልናል።

ናትናኤል ወልዴ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ሸዋዬ ለገሰ