ኢትዮጵያ የብር ሜዳልያ አገኘች
ረቡዕ፣ ነሐሴ 30 2004ማስታወቂያ
ለንደን ውስጥ በመካሄድ ላይ ባለው የፓራሊምፒክስ ውድድር ኢትዮጵያ ትንንት ምሽት በተካሄደ የሩጫ ውድድር የመጀመሪያውን ሜዳልያ አገኘች ። በትናንቱ የ1500 ሜትር የአንድ እጅ አካል ጉዳተኞች የሩጫ ውድድር የ 24 አመቱ ወንድዮ ፍቅሬ እንደልቡ 2ተኛ በመውጣት ለኢትዮጵያ የብር ሜዳልያ አስግኝቷል ። በዚሁ ውድድር ኬንያ የወርቅ አልጀሪያ ደግሞ የነሐስ ሜዳልያ ወስደዋል ። በስፍራው የምትገኘው ሃይማኖት ጥሩነህ ዝርዝሩን ልካልናለች ።
ሃይማኖት ጥሩነህ
ሂሩት መለሰ
ተክሌ የኋላ