1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢትዮጵያ እና የድህነት ቅነሳው ሂደት

ሰኞ፣ የካቲት 2 2007

በኢትዮጵያ ካለፉት ጥቂት ዓመታት ወዲህ የድህነት መጠን መቀነሱን የዓለም ባንክ ከጥቂት ሳምንታት በፊት ማስታወቁ ይታወሳል። ባንኩ ባወጣው ዘገባ ፣ ፈጣን የኤኮኖሚ እድገት በማሳየት ላይ ባለችው ኢትዮጵያ ድህነት በ30% ነው የቀነሰው። ያም ቢሆን ግን፣ አንድ ሦስተኛው የሀገሪቱ ሕዝብ አሁንም በከፋ ድህነት ውስጥ እንደሚገኝ

https://p.dw.com/p/1EXV6
Karte Äthiopien englisch

እና ወደ ድህነት አዘቅትየመውደቅ ስጋት እንደተደቀነበት የባንኩ ዘገባ ገልጾዋል። የዓለም ባንክ ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር በመተባበር አሰናዳሁት ባለው እና ከጥቂት ሳምንታት በፊት ባወጣው የቅርብ ጊዜ ዘገባው መሠረት በኢትዮጵያ የድህነት መጠን ቀንሶ በ2003 እና 2004 ዓም 30 ከመቶ መድረሱን ገልጧል። ሆኖም የዓለም ባንክ በዚሁ ዘገባው በኢትዮጵያ 37 ሚሊዮን የሚገመት ሕዝብ በድህነት አረንቋ ውስጥ እንደሚገኝ እና ወደ ድህነት አዘቅት የመውደቅ ስጋት እንደተደቀነበትም አስታውቋል። ባንኩ ባወጣው ዘገባ፣ ፈጣን የኤኮኖሚ እድገት እያሳየች ነው ባላት ኢትዮጵያ ውስጥ እጅግ ድሀ የነበሩ ሰዎች ይበልጥ መደኽየታቸውንም አስገንዝቧል። የዓለም ባንክ ስላወጣው የድህነት ቅነሳ ዘገባ ውይይት አካሂደናል።

አርያም ተክሌ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ