ኢትዮጵያ እና የውጭ ምንዛሪ ክምችት እጥረት
ዓርብ፣ መስከረም 25 2005
ዕቃ ከውጭ በንግድ ለማስገባት ከባንክ ብድር የሚጠይቁ ነጋዴዎች ባንኮቹ በቂ የውጭ ምንዛሪ ክምችት ስለሌላቸው የውጭ ምንዛሪ ብድር መጠየቂያ ማመልከቻ አስገብተው ወረፋ መያዝ በመገደዳቸው ቅር መሰኘታቸውን በመግለጽ ይህ ሁኔታ ቀደም ብሎ ይፋ ቢነራቸው ኖሮ፣ አንዳንድ ቅድመ ዝግጅት ሊያደርጉ ይችሉ እንደነበር አስታውቀዋል። ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ትልቁ የውጭ ምንዛሪ ገዢ የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከሁለት እስከ ሦስት ወራት ለሆነ ጊዜ ብድር መስጠቱን እንደሚያቋርጥ ባለፈው ነሀሴ ወር ማስታወቁ የሚታወስ ነው። በያመቱ በድርጅቱ መመሪያ ደንብ አንቀጽ አራት መሠረት ከአባል ሀገራት ጋ ምክክር የሚያካሂደው የዓለም አቀፉ የገንዘብ መርህ ድርጅት፡ አይ ኤም ኤፍ ጠበብት ከጥቂት ጊዜ በፊት ወደ ኢትዮጵያ መጥተውና ጥናት አካሂደው ከተመለሱ በኋላ ባለፈው ሰኞ ያወጡት ዘገባቸው ኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሪ ክምችቷን እንድታስተካክል ሀሳብ ያቀረቡበት ድርጊት በሀገሪቱ በርግጥ የውጭ ምንዛሪ ክምችት እጥረት መኖሩን ጠቋሚ ሆኖዋል። በወቅቱ የተከሰተው እጥረት ደረጃ በርግጥ ይህን ያህል ነው ተብሎ መናገር ባይቻልም ችግሩ አሳሳቢ መሆኑን የሣምንታዊው ጋዜጣ ፎርቹን ማኔጂንግ ኤዲተር አቶ ታምራት ገብረጊዮርጊስ ገልጾዋል።
« »
የሣምንታዊው ጋዜጣ ፎርቹን ማኔጂንግ ኤዲተር አቶ ታምራት ገብረጊዮርጊስ ለዚሁ በወቅቱ በሀገሪቱ ለሚታየው የውጭ ምንዛሪ ክምችት እጥረት መንሥዔ ሊሆኑ ይችላሉ ያሉዋቸውን ምክንያቶች እንደሚከተለው አስረድተዋል።
« »
አቶ ታምራት ገብረጊዮርጊስ እንደሚለው፡ ኢትዮጵያ በንግድ ወደ ውጭ የምትልከውን ምርት ዋጋ ማሳደግን የመሳሰሉ ርምጃዎች ይህንኑ አሳሳቢ ችግር ለማስወገድ ይችላሉ።
አርያም ተክሌ
ነጋሽ መሀመድ