1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢትዮጵያ እና የኩነቶች ምዝገባ

Merga Yonas Bulaሐሙስ፣ ሐምሌ 21 2008

የኢትዮጵያ የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ኤጀንስ ከሐምሌ 30, 2008 ዓ,ም ጀምሮ በአገር አቀፍ ደረጃ የትዉልድ ቀን፣ ሰው የሚሞትበት፣ የሚያገባበት፣ ከተፋታም የሚፋታበትን ዕለት በመመዝገብ የምስክር ወረቀት መስጠት ይጀምራል።

https://p.dw.com/p/1JXOc
Karte Äthiopien englisch

[No title]

ኤጀንስ ዉ ባወጣዉ ጋዜጣዊ መግለጫ እንደተጠቀሰው፤ ዓለም አቀፍ ደረጃን የጠበቀ ነዉ የተባለዉን ይህ የኩነቶች ምዝገባ፣ አዲስ አበባን ጨምሮ በአራት ክልሎች ላይ በቀጥታ ስርጭት ለማካሄድ ታቅዶዋል።


የኢትዮጵያ የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ኤጀንስ ከተቋቋመ ካለፉት ሦስት ዓመታት ጀምሮ፣ ምዝገባዉንና ምስክር ወረቀቶች የመስጠቱን ሥራ የሚያከናውኑ በእያንዳንዱ ዞኖች በአማካይ ሦስት ሰዎች፤ በወረዳ ሁለት፣ እንዲሁም፣ በየቀበሌዉ የክብር መዝገብ ሹም የተባሉ፤ ከ16,000 በላይ የሰዉ ኃይል እንዳዘጋጀ የኤጄንሲዉ የሕዝብ ግኑኝነትና የኮሙኒኬሼን ዳይሬክቴር አቶ ሚካኤል መንገሻ ለዶይቼ ቬሌ ተናግረዋል።


ኩነቶች እንደተከሰቱ፣ ለምሳሌ ዜጎች ልጅ መወለዱን በ90 ቀን ዉስጥ፥ ጋብቻ እና ፍች መፈፀሙን፣ ሰው ሲሞት ደግሞ በ30 ቀን ዉስጥ ማስመዝገብ ይጠበቅባቸዋል።


የኢትዮጵያ የወሳኝ ሁኔታዎች ምዝገባ ኤጀንስ መግለጫ እንደሚያሳየው፣ መስሪያ ቤቱ ዝግጅቱን በማፋጠኑ ረገድ ከተባበሩት መንግሥታት የሕጻናት መርጃ ድርጅት፣ «UNICEF» ጋርተባብሮ እየሰራ ነው።

ለተጨማር መረጃ የድምጽ ዘገባዉን ያዳምጡ።

መርጋ ዮናስ

አረያም ተክሌ