ተቃውሞ በኢትዮጵያ
እሑድ፣ ነሐሴ 8 2008ማስታወቂያ
ባለፈው ሳምንት በአማራ እና በኦሮምያ ክልሎች በተካሄዱ ሰላማዊ ሰልፎች የሰዎች ህይወት መጥፋቱ ሰልፈኞች ለከባድ ድብደባ መዳረጋቸው እና መታሰራቸው አሁንም እያነጋገረ ነው። አጀማመራቸው ሰላማዊ የነበረው እነዚህ ሰልፎች መጨረሻቸው ግድያ ድብደባ እና እሥራት መሆኑ ልዩ ልዩ ጥያቄዎችንም እያስነሳ ነው ። ሰልፎቹን በውጭ ጠላት ኃይሎች የተደረጀ » የሚለው መንግሥት ሰላማዊ ተቃውሞ ለማካሄድ አደባባይ በወጡ ሰዎች ላይ ከመጠን ያለፈ እርምጃ ነው የወሰደው ተብሏል ። ይህን የሚያጣሩ ታዛቢዎችን እንድታስገባ የተመድ የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ኢትዮጵያን ጠይቋል ። መንግሥት ሰልፎችን ለማስቆም ጠንካራ እርምጃዎች ቢወስድም የተቃውሞ ሰልፍ እንዲደረግ የሚደረገው ጥሪ እንደቀጠለ ነው ። ይህ ወዴት ያመራል ? ተጨማሪ የሰዎች ህይወት እንዳይጠፋስ ምን መደረግ አለበት ? የዛሬው እንወያይ የሚያነሳቸው ነጥቦች ናቸው ።ሙሉውን ውይይት የድምፅ ማዕቀፉን በመጫን ተከታተሉ ።
ኂሩት መለሰ
ልደት አበበ