ኢትዮጵያ፤ ተቃዋሚዎቹ ተፈቱ
ማክሰኞ፣ የካቲት 8 2008ማስታወቂያ
በአሸባሪነት ወንጀል ከተከሠሱ አምስት የኢትዮጵያ መንግሥት የተቃዋሚ ፓርቲ ፖለቲከኞች መካከል አቶ ሐብታሙ አያሌዉ እና አቶ አብረሐም ሠለሞን ዛሬ በነፃ ተለቀቁ።የአምስቱ ፖለቲከኞች ጠበቃ አቶ አመሐ መኮንን እንዳስታወቁት የደንበኞቻቸዉን ክስ ይመለከት የነበረዉ የሐገሪቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሁለቱ ፖለቲከኞች እንዲለቀቁ የወሰነዉ ባለፈዉ አርብ ነበር።ይሁንና ፖለቲከኞቹን ያሠረዉ ወሕኒ ቤት የፍርድ ቤቱን ዉሳኔ ለማክበር ሲያቅማማ ቆይቶ ዛሬ ጠዋት አሰናብቷቸዋል።የተቀሩት ሰወስቱ ፖለቲከኞች ግን ፍርድ ቤትን በመድፈር ወንጀል ሥለተፈረደባቸዉ አልተለቀቁም።የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ጠበቃ አመሐን አነጋግሯቸዋል።
ጌታቸዉ ተድላ ሐይለ ጊዮርጊስ
ነጋሽ መሐመድ
ሒሩት መለሠ