የአሜሪካ መንግሥት ማዘኑን ገለፀ
ረቡዕ፣ ነሐሴ 4 2008ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ መንግሥት የፀጥታ ሐይላት ለተቃዉሞ ሰልፍ አደባባይ የወጡ ሰላማዊ ሰዎችን መግድልና ማቁሰሉን ዩናይትድ ስቴትስ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች አወገዙ።የዋሽንግተን ዲሲ እና የአካባቢዋ ነዋሪዎች ትናንት ዩናይትድ ስቴትስ ዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር ፅሕፈት ቤት አጠገብ ባደረጉት ሠልፍ የአሜሪካ መንግሥት በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ ተፅዕኖ እንድያሳርፍ ጠይቀዋል።የዩናይትድ ስቴትስ ዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር በበኩሉ ኢትዮጵያ ዉስጥ በተደረገዉ የተቃዉሞ ሠልፍ ሰበብ ሰዎች መገደላቸዉ እንዳሳዘነዉ አስታዉቋል።በአሜሪካ ዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር የአፍሪቃ ክፍል ቃል አቀባይ የኢትዮጵያ መንግስት እና ተቃዋሚዎቹ ልዩነታቸዉን በዉይይት እንዲፈቱ አደራ ብለዋል።
መክብብ ሸዋ
ነጋሽ መሐመድ
ሒሩት መለሰ