ኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች ማህበር በዋሽንግተን ዲሲ
ሐሙስ፣ ኅዳር 2 2008ማስታወቂያ
ማህበሩ ለኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች የሥራ እድል የሚፈጠርበትን የግንኙነት መስመር የማመቻቸት ሥራ ይሠራል። በተለያዩ መሥረያ ቤቶች የሚያገለግሉ ኢትዮጵያውያን ለሌሎች ሥራ ፈላጊዎች ስልጠናና ምክር የሚሰጡበትን መድረክም ያመቻቻል። የማህበሩ መሪዎች እንደሚሉት በኮሌጆችና በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያዊ ተማሪዎች በትምህርታቸው እንዲበረቱም ያግዛል ማህበሩ። አጫጭር ስልጠና ወስደው ገቢያቸውን ለማሻሻል ለሚፈልጉ ኢትዮጵያውያንም የተመቻቹ እድሎች አሉ እንደ ማህበሩ መሪዎች ገለጻ።
በዋሽንግተን ዲሲ የሚገኘው ዘጋቢያችን የወጣት ኢትዮጵያውያን ባለሞያዎች ማህበር እንቅስቃሴን በተመለከተ ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል።
ናትናኤል ወልዴ
ሸዋዬ ለገሠ
አርያም ተክሌ