ኢትዮጵያውያን በሳውዲ
ማክሰኞ፣ የካቲት 12 2005ማስታወቂያ
ሳውዲ አረቢያው ውስጥ ከአሰሪወቻቸውጋርበሚፈጠርአለመግባባት፣በመደብደብ፣ በመደፈርናበተዛማጅችግሮችከስራየተፈናቀሉኢትዮጵያውያንቁጥርእየጨመረ ነው ፡፡ከአሰሪዎቻቸውጋር ባለመግባባትና በመጋጨት በግፍየሚገደሉናየግድያወንጀልፈጽመዋልተብለውወህኒየሚወርዱትቁጥርምያንኑያህልከፍ ብሏል ፡፡ እነዚህ ወገኖች ለደረሰባቸው ግፍ ካሳ የሚያስጥ በአጠቃላይ መብቶቻቸውን የሚያስከብር የመንግሥት ተወካይ ባለማግኘታቸው ለልዩ ልዩ ችግሮች መጋለጣቸው መቀጠሉን ነብዩ ሲራክ ከጅዳ የላከው ዘገባ ያስረዳል ። በሌላ በኩል ደግሞ አንዳንድ ግለሶቦች በራስ ተነሳሽነት ኢትዮጵያውያኑን እንደሚረዱ ነብዩ ዘግቧል ።
ነብዩ ሲራክ
ሂሩት መለሠ
አርያም ተክሌ