ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በደቡብ አፍሪቃ
ማክሰኞ፣ ነሐሴ 8 2004ማስታወቂያ
በደቡብ አፍሪቃ የኢትዮጵያ ማኅበረሰብ ሊቀመንበር አቶ ታምሩ አበበ እንደገለፁት ከሆነ ችግሩ መከሰቱን እንደሰሙ ወደ ቦታው ሶስት የማኅበረሰቡ ተወካዮችን ቢልኩም ፖሊሶች ተወካዮቹን ሰላዮች ናችሁ በሚል እስረዋቸዋል። ይህን የኢትዮጵያውያን ስደተኞቹን ችግር በተመለከተ ስቱዲዮ ከመግባቴ በፊት ደቡብ አፍሪቃ ደውዬ ኢትዮጵያውያኑን አነጋግሬያለሁ። ካነጋገርኩዋቸው መካከል ሊምፖፖ አውራጃ ቴፍሎፕ የሚባል አካባቢ ነዋሪ በሆኑት አቶ ዳንኤል አባቾ እንጀምራለን።
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ሸዋዬ ለገሰ