ኢትዮጵያውያን ሠራተኞችና የስዑዲው አዋጅ 2 ሰኔ 2005እሑድ፣ ሰኔ 2 2005በስዑዲ ዐረቢያ በሥራ ተሠማርተው ከሚገኙት ቁጥራቸው በ 10 ሺዎች ከሚገመተው ኢትዮጵያውያን መካከል በተለያዩ ምክንያቶች ትክክለኛ መታወቂያ ሰነድ የሌላቸው ፤ እስከ ሰኔ 26 ቀን 2005 ዓ ም፤ አሟልተው ካቀረቡ ፤ የመኖሪያና የሥራ ፈቃድ እንደሚያገኙ ፤https://p.dw.com/p/18m1lምስል APማስታወቂያ የስዑዲ ዐረቢያ መንግሥት ፣ ከ 3 ሳምንት ገደማ በፊት ልዩ «የምህረት አዋጅ» አውጥቷል። በዚህ አጋጣሚ ለመጠቀም ሠራተኞቹ ከአገራቸው ኤምባሲና ቆንስላ ጽ/ቤት አፋጣኝ ትብብር ይሻሉ። ከሠራተኛና አሠሪ ውል አንስቶ ያሉት ችግሮች፣ ጊዜያዊውና ዘላቂው መፍትኄስ ምንድን ነው? በዚህ ርእሰ-ጉዳይ ላይ ሦስት እንግዶችን አነጋግረናል ። እንድታዳምጡ እንጋብዛለን። ተክሌ የኋላ አዜብ ታደሰ