ኢትዮጵያዊዉ ሳይንቲስት የዓለም ሎሬት ተባሉ8 ሰኔ 2001ሰኞ፣ ሰኔ 8 2001በአሜሪካን አገር የፖርዱ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪ የሆኑት ኢትዮጵያዊዉ የእርሻ ምሁር የዘንድሮዉ የዓለም የምግብ ሽልማት አሸናፊ ሆነዋል።https://p.dw.com/p/IAEAማስታወቂያኢትዮጵያዊዉ ሳይንቲስት ዶክተር ገቢሳ ኢጄታ ለሽልማት የበቁት ድርቅና በሽታ የማያጠቃዉ የማሽላ ዘር ባደረጉት ምርምር መፍጠር በመቻላቸዉ ነዉ። ዶክተር ገቢሳ በዚህ ጥረትና ዉጤታቸዉ የዓለም ሎሬት የሚል የክብር ማዕረግና ሁለት መቶ ሃምሳ ሺህ ዶላር ተሸላሚ ይሆናሉ። የዋሽንግተን ዲሲዉ ወኪላችን አበበ ፈለቀ ተሸላሚዉን ኢንትዮጵያዊ ሳይንቲስት አነጋግሯል። አበበ ፈለቀ/ሸዋዬ ለገሠ/አርያም ተክሌ