ኢትዮጵያዊነት ሥነ-ምግባር እስከምን?
ሐሙስ፣ ሰኔ 13 2005በዚህም ትላለች በመቀጠል አረም የሚነቀለዉ ዘር ሲዘራ ነዉ፤ ሰዎችን ከመዉቀሳችን በፊት እኛ ምን ሰጠን ብሎ ማሰቡ አስፈላጊ ነዉ። «ወንድም ጋሼ አፍሪቃ» ተብሎአል በአማርኛ«Big Brother Africa»፤ ይህን እውነተኛ የቴሌቪዥን ትዕይንት ዘንድሮ ደቡብ አፍሪቃ ላይ የተቀላቀለችዉ ኢትዮጵያዊትዋ ተሳታፊ፤ የግብረ ስጋ ግንኙነት ፈፅማለች የሚለው ዜና ከወጣ ጀምሮ፤ ኢትዮጵያውያን በሁለት ወገን፤ የከረረ የባሕል እና የሞራል ጥያቄዎችን በማንሳት እየተሟጎቱ ነው፡፡ በአገራችን ሴቶችን እንደ ግል ንብረት የማየቱ ዝንባሌ አሁንም የተቀረፈ አይመስልም፤ ቤቲ ኢትዮጵያዊት ናት እንጂ፤ የኢትዮጵያዊ ንብረት አይደለችም፤ ጉዳዩ የጾተኛነት ሁኔታም ይታይበታል፤ ቤቲ ሴት በመሆንዋ ነዉ ይህ ሁሉ ትችት የደረሰባት፤ የሚሉ አስተያየት ሰጭዎች ጥቂት አይደሉም፤ ዛሪ ያነጋገርናቸዉ የስርዓተ ጾታ ጉዳይ ባለሞያ እንደሚሉት፤ በአገራችን ከተማ አካባቢ በአንዳንዱ ወጣት ላይ የሚታየዉ ስርዓት የጎደለዉ ተግባር ሴቶችን ብቻ አይወክልም። በርግጥ ይህ ቢግ ብራዘር የተሰኘ ዝግጅት ምን ያህል ኢትዮጵያ ዉስጥ ይታወቃል? ስለ ዝግጅቱ ምንነት በግልጽ ትንታኔ ተሰቶበታል? ማኅበረሰባችን ክብርን ድጋፉ ያደረገ ሃይማኖታዊ አሻራ የሰፈረበትና የታነጸ ባሕል ያለው ነው፡፡ግን ኢትዮጵያዊ ግብረገብነት እና ጨዋነት ክብንርን የመጠበቅ ባህላችን እምን ደረጃ ላይ ይገኛል? በሌላ በኩል እዉነታዉ የሚደገፍ ባይሆንም እህት ወንድሞቻችን ላይ የሞራል ዉድቀት እንዳይደርስ ባህላችን እንዳይሸረሸር በበኩላችን ምን እያደረግን ነዉ? መገናኛ ብዙሃን፤ የትምህርት ቀቋማትና፤ የትምህርት ሥርዓታችን፤ ጠቃሚ ባህላዊ እሴቶችንን በቅርስነት እንድናቆይ ቢያስተምሩ ወጣቱ በሥነ ምግባር ታንጾ ሀገር ገንቢ ለዓለምም ጠቃሚ ዜጋ እንደሚሆን አያጠያይቅም። ስህተቶችን በመነጋገር እና በመተራረም የመፍታት ባህሪያችንን እናጎልበት ያሉንን የአራት ባለሞያዎች ሙሉ ቃለ ምልልስን፤ ከዘገባዉ ስር ያለዉን የድምፅ ማሳያ ቁልፍ በመጫን ያድምጡ።
አዜብ ታደሰ
አርያም ተክሌ