1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ኢትዮጵያዉን ሥደተኞች ተያዙ

ማክሰኞ፣ ጥር 10 2008

በጠባብ ሥፍራ አለቅጥ ተጨናንቀዉ በመጓዛቸዉ አንዳዶቹ ሥደተኞች እራሳቸዉን እስከ መሳት ደርሰዉ ነበር።ስደተኞቹን በድብቅ ሲያጓጉዞ ነበር የተባሉ ታናዛኒያዊ የመኪና ሾፌርና ረዳቱ ተይዘዋልም።

https://p.dw.com/p/1Hg3W

[No title]

የታንዛኒያ ፖሊስ የሐገሪቱን ድንበር አቋርጠዉ «ማላዊ ለመግባት የሞከሩ» ያላቸዉን ከ80 በላይ ኢትዮጵያዉን ሥደተኞች መያዙን አስታወቀ። የታንዛያ ፖሊስ አዛዦች እንደሚሉት ሥደተኞቹ የታዙት በአንድ ሽፍን የጭነት መኪና ተፋፍገዉ ተጭነዉ ሲጓዙ ነዉ። በጠባብ ሥፍራ አለቅጥ ተጨናንቀዉ በመጓዛቸዉ አንዳዶቹ ሥደተኞች እራሳቸዉን እስከ መሳት ደርሰዉ ነበር።ስደተኞቹን በድብቅ ሲያጓጉዞ ነበር የተባሉ ታናዛኒያዊ የመኪና ሾፌርና ረዳቱ ተይዘዋልም። ኢትዮጵያዉን ስደተኞች ወደ ደቡብ አፍሪቃ ለመጓዝ ሲሞክሩ በተለያዩ የምሥራቅና የደቡባዊ አፍሪቃ ሐገራት ዉስጥ ይሞታሉ አለያም ይይዛሉ። ናይሮቢ የሚገኘዉን ተባባሪ ዘገቢያችንን ፋሲል ግርማን ሥለ ሥደተኞቹ ሁኔታና ጉዞ በሥልክ አነጋግሬዉ ነበር።

ፋሲል ግርማ

ነጋሽ መሐመድ

ጎይቶም ቢሆን