1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ውይይቱ ኢትዮጵያ ገጥመዋታል በተባሉ ችግሮች ላይ ተነጋግሯል።

ሰኞ፣ ታኅሣሥ 2 2010

ኢትዮጵያ የሊቢያ እጣ ፈንታ ሊገጥማት ይችላል? ተቃዋሚው ሰማያዊ የፖለቲካ ፓርቲ በሳምንቱ መገባደጃ ባካሔደው የውይይት መድረክ የተሳተፉ አንድ ግለሰብ ይኸ ሥጋት አድሮባቸዋል። የውይይቱ ተሳታፊ የኢትዮጵያ እጣ ፈንታ በሊቢያ እና በሶማሊያ መንገድ ላለመጓዙ ማንም የሚያውቅ የለም ሲሉ ተደምጠዋል።

https://p.dw.com/p/2pAd6
Demonstration der Semayawi-Partei in Addis Ababa Äthiopien 22.09.2013
ምስል DW

ሰማያዊ ፓርቲ ያዘጋጀው የአዲስ አበባ ውይይት


ኢትዮጵያ የሊቢያ እጣ ፈንታ ሊገጥማት ይችላል? ተቃዋሚው ሰማያዊ የፖለቲካ ፓርቲ በሳምንቱ መገባደጃ  ባካሔደው የውይይት መድረክ የተሳተፉ አንድ ግለሰብ ይኸ ሥጋት አድሮባቸዋል። የውይይቱ ተሳታፊ የኢትዮጵያ እጣ ፈንታ በሊቢያ እና በሶማሊያ መንገድ ላለመጓዙ ማንም የሚያውቅ የለም ሲሉ ተደምጠዋል። "ኢትዮጵያን ማን ይታደጋት?" በሚል መሪ ቃል በተካሔደው ውይይት ላይ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም እና ዶ/ር ያዕቆብ ኃይለማርያምን ጨምሮ ጉዳዩ ያሳሰባቸው ዜጎች ታድመውታል። ውይይቱ ኢትዮጵያ ገጥመዋታል በተባሉ ችግሮች ላይ ተነጋግሯል። ተመሳሳይ ውይይቶች በወርኃ ታኅሳስ በተከታታይ እንደሚደረጉ ፓርቲው አስታውቋል። 
ጌታቸው ተድላ ኃይለጊዮርጊስ
እሸቴ በቀለ 
አርያም ተክሌ