ኢትዮጵያና የአዉሮጳ ሕብረት
ማክሰኞ፣ መጋቢት 9 2006ማስታወቂያ
በኢትዮጵያ የአዉሮጳ ሕብረት አምባሳደር ወይዘሮ ቻንታል ሒብሪክት ሰሞኑን ከኢትዮጵያ መንግሥትና ከመንግሥት ተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች ጋር በየተራ ተወያይተዋል።አምባሳደሯ ከኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር ከአቶ ሐይለማርያም ደሳለኝና ከተቃዋሚ ፓርቲዎች በተለይም ከአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር ያደረጉት ዉይይት የኢትዮጵያን የፓለቲካ የሠብአዊ መብትና የዴሞክራሲ ይዞታን፤ የእስረኞች ሁኔታን የሚመለከት እንደነበር የተለያዩ መገናኛ ዘዴዎች ዘግበዋል።የአዉሮጳ ሕብረት የዉጪ ግንኙነት ቢሮ ዋና ቃል አቀባይ ማይክ ማን ግን ዉይይቱን ሁል ጊዜ የሚደረግ በማለት ገልፀዉታል።ቃል አቀባዩ በዉይይቱ የተነሱትን ዝርዝር ጉዳዮች መግለፅም አልፈለጉም።የብራስልሱ ወኪላችን ገበያዉ ንጉሴ ቃል አቀባይ ማንን አነጋግሮ የሚከተለዉን ዘገባ ልኮልናል።
ገበያዉ ንጉሴ
ነጋሽ መሐመድ
አርያም ተክሌ